am_tn/exo/29/01.md

1.2 KiB

• የምታደርግባቸው ነገር ይህ ነው

እግዚአብሔር የካህናት ልብስ ዝግጅትና አሰራር ላይ የሰጠውን መመሪያ ጨርሶ ወደ ካህናትን ወደ መቀደስ ሥርዓት ሲሻገር እናያለን።

• የምታደርግባቸው ነገር ይህ ነው

ይህን የሚሰራው ሙሴ እንደ ሆነ ማመልከቱ ነው።

• ትቀድሳቸው ዘንድ

አሮንና ልጆቹ ካህናት ሆነው በፊቴ ወይም እኔን እንዲያገለግሉኝ የምትለያቸው

• እንዲያገለግሉኝ

በአንደኛ መደብ የተገለጸው እግዚአብሔር /ያህዌ/ ነው። በሌላ አገላለጽ፦ “እኔን እንዲያገለግሉ”

• አንድ ወይፈን

ቀንበር ያልተቀመጠበት ወጣት በሬ ማለት ነው

• ቂጣ እንጀራ፥ በዘይትም የተለወሰ የቂጣ እንጎቻ

እርሾ ያልነካው በወይራ ዘይት የታሸ ወይም ወይራ ዘይት የመጨመረበት ቂጣ

• በዘይትም የተቀባ ስስ ቂጣ ከመልካም ስንዴ

ምርጥ የሆነ የስንዴ ዱቄት ወስደህ ስስ/ቀጭን/ ቂጣ ጋግረህ ዘይት ቀባው