am_tn/2ki/02/11.md

1.1 KiB

እነሆ

እዚህ ላይ፣ ‹‹እነሆ›› የሚለው ቃል ቀጥሎ ያለውን አስደናቂ ነገር በንቃት መጠበቅ እንዳለብን ያመለክታል፡፡

የእሳት ሠረገላና የእሳት ፈረሶች

‹‹የእሳት›› የሚለው በእሳት መከበባቸውን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በእሳ የተከበበ ሠረገላና በእሳት የተከበቡ ፈረሶች››

በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ዐረገ

‹‹በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ተወሰደ፡፡›› ‹‹ዐውሎ ነፋስ›› የሚለውን ቃል 2 ነገሥት 2፥1 ስትተረጉም በተጠቀምህበት ቃል ተርጉመው፡፡

አባቴ! አባቴ!

ኤልሳዕ የሚያከብረውን መሪ እየተጣራ ነው፡፡

ከሁለት ቦታ ቀደደ

ብዙውን ጊዜ ሰዎች ልብሳቸውን የሚቀዱት በጣም ለማዘናቸውና ለመተከዛቸው ምልክት እንዲሆን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ምን ያህል ማዘኑን ለማሳየት ሁለት ቦታ ቀደደው››