# እነሆ እዚህ ላይ፣ ‹‹እነሆ›› የሚለው ቃል ቀጥሎ ያለውን አስደናቂ ነገር በንቃት መጠበቅ እንዳለብን ያመለክታል፡፡ # የእሳት ሠረገላና የእሳት ፈረሶች ‹‹የእሳት›› የሚለው በእሳት መከበባቸውን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በእሳ የተከበበ ሠረገላና በእሳት የተከበቡ ፈረሶች›› # በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ዐረገ ‹‹በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ተወሰደ፡፡›› ‹‹ዐውሎ ነፋስ›› የሚለውን ቃል 2 ነገሥት 2፥1 ስትተረጉም በተጠቀምህበት ቃል ተርጉመው፡፡ # አባቴ! አባቴ! ኤልሳዕ የሚያከብረውን መሪ እየተጣራ ነው፡፡ # ከሁለት ቦታ ቀደደ ብዙውን ጊዜ ሰዎች ልብሳቸውን የሚቀዱት በጣም ለማዘናቸውና ለመተከዛቸው ምልክት እንዲሆን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ምን ያህል ማዘኑን ለማሳየት ሁለት ቦታ ቀደደው››