am_tn/1ki/15/27.md

21 lines
1.3 KiB
Markdown

# በናዳብ ላይ አሴረ
"ንጉሥ ናዳብን ለመግደል በምስጢር አሴረ/ተንኮል ጠነሰሰ"
# ገባቶን
ይህ የከተማ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
# ናዳብ እና መላው እስራኤል
"መላው እስራኤል" የሚለው ሀረግ ከእስራኤል ወታደሮች አመዛኙን የሚወክል ነው፡፡ "ናዳብ እና በርካታው እስራኤል ወታደር" ወይም "ናዳብ እና የእስራኤል ሰራዊት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ እናኩሸት እንደዚሁም አጠቃላይ አስተያየት የሚሉትን ይመልከቱ)
# ገባቶንን ከበው ነበር
"ስለዚህም የገባቶን ሰዎች ለእነርሱ እጃቸውን እንዲሰጡ፣ ከተማይቱን ከበው ነበር"
# በእርሱ ስፍራ ነገሠ
"በእርሱ ስፍራ" የሚለው ሀረግ ዘይቤያዊ አነጋገር ሲሆን ትርጉሙ "በእርሱ ምትክ" ማለት ነው፡፡"
"በናዳብ ምትክ ንጉሥ ሆነ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)