16 lines
976 B
Markdown
16 lines
976 B
Markdown
|
# የብርታቴ አምላክ
|
||
|
|
||
|
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፣ 1) “የሚጠብቀኝ አምላክ” ወይም 2) “ብርታት የሚሰጠኝ አምላክ” የሚሉት ናቸው።
|
||
|
|
||
|
# ለምን ተውከኝ? በጠላት ጭቆና ምክንያት ለምን እያለቀስኩ እሄዳለሁ?
|
||
|
|
||
|
ጸሐፊው እነዚህን ጥያቄዎች የሚጠይቀው ምላሽ ለማግኘት ሳይሆን በእግዚአብሔር ላይ ያለውን ቅሬታና ስሜቱን ለመግለጽ ነው። (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
|
||
|
|
||
|
# ለምን እያለቀስኩ እሄዳለሁ
|
||
|
|
||
|
“እያለቀሱ መሄድ” በጣም ከማዘን ጋር የተያያዘ ሥርዓት መፈጸም ነው።
|
||
|
|
||
|
# በጠላት ጭቆና ምክንያት
|
||
|
|
||
|
“ጭቆና” የሚለው ቃል እንደ ግሥ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ጠላቴ ስለሚጨቁነኝ” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
|