# የብርታቴ አምላክ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፣ 1) “የሚጠብቀኝ አምላክ” ወይም 2) “ብርታት የሚሰጠኝ አምላክ” የሚሉት ናቸው። # ለምን ተውከኝ? በጠላት ጭቆና ምክንያት ለምን እያለቀስኩ እሄዳለሁ? ጸሐፊው እነዚህን ጥያቄዎች የሚጠይቀው ምላሽ ለማግኘት ሳይሆን በእግዚአብሔር ላይ ያለውን ቅሬታና ስሜቱን ለመግለጽ ነው። (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት) # ለምን እያለቀስኩ እሄዳለሁ “እያለቀሱ መሄድ” በጣም ከማዘን ጋር የተያያዘ ሥርዓት መፈጸም ነው። # በጠላት ጭቆና ምክንያት “ጭቆና” የሚለው ቃል እንደ ግሥ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ጠላቴ ስለሚጨቁነኝ” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)