am_tw/bible/kt/honor.md

1000 B

ክብር፣ ማክበር

“ክብር” የሚለው ቃል ለእግዚአብሔር ወይም ለሰው ልጅ የሚሰጥ የላቀ ቦታ፣ ግምት ወይም አክብሮታዊ ፍርሃት ነው።

  • ሌሎችን እንዲያከብሩ ለራሳቸው ግን ክብር መፈለግ እንደሌለባቸው እግዚአብሔር ለክርስቲያኖች ተናግሮአል።
  • ልጆች ወላጆቻቸውን እንዲያከብሩ ተነግሮአቸዋል፤ ይህም መታዘዝንም ይጨምራል።
  • በተለይ ስለ ኢየሱስ በሚነገርበት ጊዜ፣ “ክብርና ግርማ” በአንድነት ተያይዘው ይቀርባሉ። አንድን ነገር የሚያመለክቱ ሁለት የተለያዩ የአገላለጽ መንገዶችን የሚያመለክቱ ሊሆኑ ይችላሉ።
  • እግዚአብሔርን ማክበር ለእርሱ መታዘዝንና የእርሱን ታላቅነት በሚያሳይ መንገድ መኖርንም ያጠቃልላል፥