# ክብር፣ ማክበር “ክብር” የሚለው ቃል ለእግዚአብሔር ወይም ለሰው ልጅ የሚሰጥ የላቀ ቦታ፣ ግምት ወይም አክብሮታዊ ፍርሃት ነው። * ሌሎችን እንዲያከብሩ ለራሳቸው ግን ክብር መፈለግ እንደሌለባቸው እግዚአብሔር ለክርስቲያኖች ተናግሮአል። * ልጆች ወላጆቻቸውን እንዲያከብሩ ተነግሮአቸዋል፤ ይህም መታዘዝንም ይጨምራል። * በተለይ ስለ ኢየሱስ በሚነገርበት ጊዜ፣ “ክብርና ግርማ” በአንድነት ተያይዘው ይቀርባሉ። አንድን ነገር የሚያመለክቱ ሁለት የተለያዩ የአገላለጽ መንገዶችን የሚያመለክቱ ሊሆኑ ይችላሉ። * እግዚአብሔርን ማክበር ለእርሱ መታዘዝንና የእርሱን ታላቅነት በሚያሳይ መንገድ መኖርንም ያጠቃልላል፥