am_tw/bible/kt/holyspirit.md

1.3 KiB

መንፈስ ቅዱስ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ፣ የጌታ መንፈስ

እነዚህ ሦስት ቃሎች የሚያመለክቱት እርሱ ራሱ እግዚአብሔር የሆነው መንፈስ ቅዱስን ነው። እውነተኛው አንድ አምላክ አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ የሚባሉ አካላት አሉት።

  • መንፈስ ቅዱስ አንዳንዴ፣ “መንፈስ” እና “የያህዌ መንፈስ” እና፣ “የእውነት መንፈስ” ተብሏል።
  • መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር በመሆኑ ፍጹም ቅዱስ፣ እጅግ ንጹሕ፣ በባሕርዩና በሚያደርገው ነገር ሁሉ ፍጹም ጻድቅ ነው።
  • ከአብና ከወልድ ጋር መንፈስ ቅዱስ ዓለምን በመፍጠር ተሳታፊ ነበር።
  • እግዚአብሔር ወልድ ማለት ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከተመለሰ በኋላ ሕዝቡን እንዲመራቸው፣ እንዲያስተምራቸው፣ እንዲያጽናናቸውና የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማድረግ እንዲያስችላቸው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ላከ።
  • መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን መራው፤ በኢየሱስ የሚያምኑትንም ይመራቸዋል።