am_tw/bible/kt/holyspirit.md

10 lines
1.3 KiB
Markdown
Raw Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# መንፈስ ቅዱስ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ፣ የጌታ መንፈስ
እነዚህ ሦስት ቃሎች የሚያመለክቱት እርሱ ራሱ እግዚአብሔር የሆነው መንፈስ ቅዱስን ነው። እውነተኛው አንድ አምላክ አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ የሚባሉ አካላት አሉት።
* መንፈስ ቅዱስ አንዳንዴ፣ “መንፈስ” እና “የያህዌ መንፈስ” እና፣ “የእውነት መንፈስ” ተብሏል።
* መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር በመሆኑ ፍጹም ቅዱስ፣ እጅግ ንጹሕ፣ በባሕርዩና በሚያደርገው ነገር ሁሉ ፍጹም ጻድቅ ነው።
* ከአብና ከወልድ ጋር መንፈስ ቅዱስ ዓለምን በመፍጠር ተሳታፊ ነበር።
* እግዚአብሔር ወልድ ማለት ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከተመለሰ በኋላ ሕዝቡን እንዲመራቸው፣ እንዲያስተምራቸው፣ እንዲያጽናናቸውና የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማድረግ እንዲያስችላቸው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ላከ።
* መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን መራው፤ በኢየሱስ የሚያምኑትንም ይመራቸዋል።