am_tw/bible/kt/heaven.md

9 lines
1.3 KiB
Markdown

# ሰማይ፣ ሰማያት፣ ሰማያዊ
“ሰማይ” ተብሎ የተተረጎመው ቃል የእግዚአብሔር መኖሪያን ያመለክታል።
* “ሰማያት” የሚለው ቃል ፀሐይ፣ ጨረቃንና ከዋክብትን ጨምሮ ከምድር በላይ የምንመለከተውን ማንኛውንም ነገር ያመለክታል። ምድር ላይ ሆነን በቀጥታ የማናያቸውን በሩቅ ያሉ ፕላኔቶችን ጨምሮ የሰማይ አካላትን ሁሉ ያጠቃልላል።
* “ሰማይ” ደመናና የምንተነፍሰው አየር ያለበትን ከምድር በላይ ያለውን የተንጣለለ ሰማያዊ ቦታ ያመለክታል። ብዙውን ጊዜ ፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት፣ “በላይ በሰማይ” መሆናቸው ይነገራል።
* በአንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ዐውዶች መሠረት “ሰማይ” እንዲሁ ከምድር በላይ የተንጣለለው ሰማያዊ ቦታ ወይም የእግዚአብሔርን መኖሪያ ያመለክታል።
* “ሰማይ” በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ የሚውለው እግዚአብሔርን ለማመልከት ነው። ለምሳሌ ማቴዎስ ስለ “መንግሥተ ሰማይ” ሲናገር ስለ፣ “የእግዚአብሔር መንግሥት” መናገሩ ነው።