# ሰማይ፣ ሰማያት፣ ሰማያዊ “ሰማይ” ተብሎ የተተረጎመው ቃል የእግዚአብሔር መኖሪያን ያመለክታል። * “ሰማያት” የሚለው ቃል ፀሐይ፣ ጨረቃንና ከዋክብትን ጨምሮ ከምድር በላይ የምንመለከተውን ማንኛውንም ነገር ያመለክታል። ምድር ላይ ሆነን በቀጥታ የማናያቸውን በሩቅ ያሉ ፕላኔቶችን ጨምሮ የሰማይ አካላትን ሁሉ ያጠቃልላል። * “ሰማይ” ደመናና የምንተነፍሰው አየር ያለበትን ከምድር በላይ ያለውን የተንጣለለ ሰማያዊ ቦታ ያመለክታል። ብዙውን ጊዜ ፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት፣ “በላይ በሰማይ” መሆናቸው ይነገራል። * በአንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ዐውዶች መሠረት “ሰማይ” እንዲሁ ከምድር በላይ የተንጣለለው ሰማያዊ ቦታ ወይም የእግዚአብሔርን መኖሪያ ያመለክታል። * “ሰማይ” በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ የሚውለው እግዚአብሔርን ለማመልከት ነው። ለምሳሌ ማቴዎስ ስለ “መንግሥተ ሰማይ” ሲናገር ስለ፣ “የእግዚአብሔር መንግሥት” መናገሩ ነው።