991 B
991 B
ልብ
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ልብ የሰውን ሐሳብ፣ ስሜት፣ ፍላጎት ወም ፈቃድ ለማመልከት ብዙውን ጊዜ በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል።
- “ልበ ጠንካራ” መሆን ሰውየው በግትርነት ለእግዚአብሔር መታዘዝ አለመፈለጉን የሚያሳይ የተለመደ አገላለጽ ነው።
- “በፍጹም ልቤ” ወይም፣ “በሙሉ ልቤ” የተሰኙት አገላለጾች ምንም ወደ ኋላ ሳይባል፣ በሙሉ መሰጠትና ፈቃደኛነት አንድን ነገር ማድረግን ያመለክታሉ።
- “በልብህ ያዘው” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ለአንድ ሰው የተለየ ከበሬታ መስጠት ማለት ነው።
- “ልበ ሰባራ” የሚለው ሐረግ ከፍ ያለ ሐዘንን ያመለክታል። የሰውየው ስሜት በከፍተኛ ደረጃ ተጎድቷል ማለት ነው።