am_tw/bible/kt/heart.md

9 lines
991 B
Markdown
Raw Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ልብ
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ልብ የሰውን ሐሳብ፣ ስሜት፣ ፍላጎት ወም ፈቃድ ለማመልከት ብዙውን ጊዜ በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል።
* “ልበ ጠንካራ” መሆን ሰውየው በግትርነት ለእግዚአብሔር መታዘዝ አለመፈለጉን የሚያሳይ የተለመደ አገላለጽ ነው።
* “በፍጹም ልቤ” ወይም፣ “በሙሉ ልቤ” የተሰኙት አገላለጾች ምንም ወደ ኋላ ሳይባል፣ በሙሉ መሰጠትና ፈቃደኛነት አንድን ነገር ማድረግን ያመለክታሉ።
* “በልብህ ያዘው” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ለአንድ ሰው የተለየ ከበሬታ መስጠት ማለት ነው።
* “ልበ ሰባራ” የሚለው ሐረግ ከፍ ያለ ሐዘንን ያመለክታል። የሰውየው ስሜት በከፍተኛ ደረጃ ተጎድቷል ማለት ነው።