am_tw/bible/kt/goodnews.md

788 B

የምሥራች፣ ወንጌል

ቃል በቃል የምሥራች ማለት ሲሆን፣ ሰዎችን የሚጠቅምና ደስ የሚያሰኛቸውን መልእክት ያመለክታል።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙውን ጊዜ ይህ ቃል የሚያመለክተው በኢየሱስ መስቀል ላይ መሥዋዕት መሆን አማካይነት እግዚአብሔር ለሰዎች ያለውን ድነት ነው።
  • በአብዛኞቹ የአማርኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች “የምሥራች” የሚለው ቃል፣ “ወንጌል” ተብሎ ተተርጉሞአል። ለምስሌ፣ “የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል” እና፣ “የመንግሥቱ ወንጌል” ከተሰኙት ሐረጎች መመልከት ይቻላል።