# የምሥራች፣ ወንጌል ቃል በቃል የምሥራች ማለት ሲሆን፣ ሰዎችን የሚጠቅምና ደስ የሚያሰኛቸውን መልእክት ያመለክታል። * መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙውን ጊዜ ይህ ቃል የሚያመለክተው በኢየሱስ መስቀል ላይ መሥዋዕት መሆን አማካይነት እግዚአብሔር ለሰዎች ያለውን ድነት ነው። * በአብዛኞቹ የአማርኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች “የምሥራች” የሚለው ቃል፣ “ወንጌል” ተብሎ ተተርጉሞአል። ለምስሌ፣ “የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል” እና፣ “የመንግሥቱ ወንጌል” ከተሰኙት ሐረጎች መመልከት ይቻላል።