am_tw/bible/kt/godthefather.md

1.2 KiB

እግዚአብሔር አብ፣ ሰማያዊ አባት፣ አባት

“እግዚአብሔር አብ” እና፣ “ሰማያዊ አባት” የተሰኙት ቃሎች የሚያመለክቱት አንዱን እውነተኛ አምላክ ያህዌን ነው። ይህ ቃል በተለይም ኢየሱስ ሲጠቀምበት “አባት” ተብሎም ተጠርቷል።

  • እግዚአብሔር - እግዚአብሔር አብ፣ እግዚአብሔር ወልድና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ተብሎ ተጠርቷል። እያንዳንዱ አካል ፍጹም አምላክ ነው፤ ይሁን እንጂ ያለው አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ይህ ሰዎች ሙሉ በሙሉ መረዳት የማይችሉት ምስጢር ነው።
  • እግዚአብሔር አብ እግዚአብሔር አልድን (ኢየሱስን) ወደ ዓለም ላከ እርሱም መንፈስ ቅዱስን ለሕዝቡ ላከ።
  • በእግዚአብሔር ወልድ የሚያምን ሁሉ የእግዚአብሔር አብ ልጅ ይሆናል፤ መንፈስ ቅዱስ በዚያ ሰው ውስጥ ለመኖር ይመጣል። ይህ የሰው ልጅ ሙሉ በሙሉ መረዳት የማይችለው ምስጢር ነው።