# እግዚአብሔር አብ፣ ሰማያዊ አባት፣ አባት “እግዚአብሔር አብ” እና፣ “ሰማያዊ አባት” የተሰኙት ቃሎች የሚያመለክቱት አንዱን እውነተኛ አምላክ ያህዌን ነው። ይህ ቃል በተለይም ኢየሱስ ሲጠቀምበት “አባት” ተብሎም ተጠርቷል። * እግዚአብሔር - እግዚአብሔር አብ፣ እግዚአብሔር ወልድና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ተብሎ ተጠርቷል። እያንዳንዱ አካል ፍጹም አምላክ ነው፤ ይሁን እንጂ ያለው አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ይህ ሰዎች ሙሉ በሙሉ መረዳት የማይችሉት ምስጢር ነው። * እግዚአብሔር አብ እግዚአብሔር አልድን (ኢየሱስን) ወደ ዓለም ላከ እርሱም መንፈስ ቅዱስን ለሕዝቡ ላከ። * በእግዚአብሔር ወልድ የሚያምን ሁሉ የእግዚአብሔር አብ ልጅ ይሆናል፤ መንፈስ ቅዱስ በዚያ ሰው ውስጥ ለመኖር ይመጣል። ይህ የሰው ልጅ ሙሉ በሙሉ መረዳት የማይችለው ምስጢር ነው።