am_tw/bible/kt/gift.md

9 lines
849 B
Markdown

# ስጦታ
“ስጦታ” የሚለው ለሌላው ወገን የተሰጠ ማንኛውንም ነገር ያመለክታል። ስጦታ የሚሰጠው በምላሹ ምንም ነገር ባለ መጠበቅ ነው።
* ለድኾች የሚሰጥ ገንዘብ፣ ምግብ፣ ልብስና ማንኛውም ነገር “ስጦታ” ይባላል።
* መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለእግዚአብሔር የሚሰጥ መባ ወይም መሥዋዕትም፣ “ስጦታ” ይባላል።
* የድነት ስጦታ በኢየሱስ በማመን በኩል እግዚአብሔር የሰጥን ነው።
* አዲስ ኪዳን ውስጥ፣ “ስጦታ” የሚለው ቃል ሌሎችን ለማገልገል እግዚአብሔር ለክርስቲያኖች ሁሉ ይሚሰጠውን የተለያዩ መንፈሳዊ ችሎታዎችን ያመለክታል።