am_tw/bible/kt/gift.md

849 B

ስጦታ

“ስጦታ” የሚለው ለሌላው ወገን የተሰጠ ማንኛውንም ነገር ያመለክታል። ስጦታ የሚሰጠው በምላሹ ምንም ነገር ባለ መጠበቅ ነው።

  • ለድኾች የሚሰጥ ገንዘብ፣ ምግብ፣ ልብስና ማንኛውም ነገር “ስጦታ” ይባላል።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለእግዚአብሔር የሚሰጥ መባ ወይም መሥዋዕትም፣ “ስጦታ” ይባላል።
  • የድነት ስጦታ በኢየሱስ በማመን በኩል እግዚአብሔር የሰጥን ነው።
  • አዲስ ኪዳን ውስጥ፣ “ስጦታ” የሚለው ቃል ሌሎችን ለማገልገል እግዚአብሔር ለክርስቲያኖች ሁሉ ይሚሰጠውን የተለያዩ መንፈሳዊ ችሎታዎችን ያመለክታል።