am_tw/bible/kt/gentile.md

10 lines
1.3 KiB
Markdown

# አሕዛብ
አሕዛብ የያዕቆብ ወይም የአሥራ ሁለቱ የእርሱ ልጆች ዘር ያልሆነ ሰው ነው። ስለሆነም አሕዛብ አይሁድ አይድለም ማለት ነው።
* ቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ አሕዛብ አልፎ አልፎ፣ “ያልተገረዙ” ተብለው ይጠራሉ፤ ምክንያቱም እስራኤላውያን እንደሚያደርጉት አብዛኞቹ ወንዶች ልጆቻቸውን ስለማይገርዙ ነው።
* ያ እርሱ የተለየ ሕዝብ እንደሆኑ እግዚአብሔር አይሁድን በመምረጡ፣ አሕዛብ ባዕዳንና የእግዚአብሔር ሕዝብ መሆን እንደማይችሉ አሰቡ።
* በታሪክ ውስጥ በተለያየ ጊዜ አይሁድም እስራኤላውያን ወይም ዕብራውያን ተብለው ተጠርተዋል። ሌሎች ግን አሕዛብ ተብለው የሚጠሩት።
* አሕዛብ የሚለውን፣ “አይሁድ ያልሆነ” ወይም፣ “እስራኤላዊ ያልሆነ” (ብሉይ ኪዳን) ብሎ መተርጎም ይቻላል።
* በባሕላቸው መሠረት አይሁድ ከአሕዛብ ጋር አይበሉም ነበር፤ ይህም በጥንት ቤተ ክርስቲያን ችግር ሆኖ ነበር።