am_tw/bible/kt/fellowship.md

1.2 KiB

ኅብረት

አጠቃላይ በሆነ ደረጃ፣ “ኅብረት” ተመሳሳይ ፍላጎትና ልምምድ ያላቸው የአንድ ማኅበር አባሎች መካከል የሚደረግ የወዳጅነት ግንኙነትን ያመለክታል።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ኅብረት” በክርስቶስ የሚያምኑ ሰዎች አድነትን ነው ምንጊዜም የሚያመለክተው።
  • ክርስቲያናዊ ኅብረት ከክርስቶስና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ባላቸው ግንኙነት አመካይነት አማኞች እርስበርስ ያላቸውን ግንኙነት የሚገልጹበት መንገድ ነው።
  • የጥንት ክርስቲያኖች ኅብረታቸውን የሚገልጹት የእግዚአብሔርን ቃል ትምህርት በመካፈል፣ በአንድነት በመጸለይ ያላቸውን ሁሉ በመካፈልና አብረው በመመገብ ነበር።
  • ክርስቲያኖች በኢየሱስ፣ በሰዎችና በእግዚአብሔር መካከል የነበረውን መለያየት ባስወገደበት የመስቃል ላይ መሥዋዕታዊ ሞቱ በማመናቸው ከእግዚአብሔርም ጋር ኅብረት አላቸው።