# ኅብረት አጠቃላይ በሆነ ደረጃ፣ “ኅብረት” ተመሳሳይ ፍላጎትና ልምምድ ያላቸው የአንድ ማኅበር አባሎች መካከል የሚደረግ የወዳጅነት ግንኙነትን ያመለክታል። * መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ኅብረት” በክርስቶስ የሚያምኑ ሰዎች አድነትን ነው ምንጊዜም የሚያመለክተው። * ክርስቲያናዊ ኅብረት ከክርስቶስና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ባላቸው ግንኙነት አመካይነት አማኞች እርስበርስ ያላቸውን ግንኙነት የሚገልጹበት መንገድ ነው። * የጥንት ክርስቲያኖች ኅብረታቸውን የሚገልጹት የእግዚአብሔርን ቃል ትምህርት በመካፈል፣ በአንድነት በመጸለይ ያላቸውን ሁሉ በመካፈልና አብረው በመመገብ ነበር። * ክርስቲያኖች በኢየሱስ፣ በሰዎችና በእግዚአብሔር መካከል የነበረውን መለያየት ባስወገደበት የመስቃል ላይ መሥዋዕታዊ ሞቱ በማመናቸው ከእግዚአብሔርም ጋር ኅብረት አላቸው።