am_tw/bible/kt/fear.md

8 lines
927 B
Markdown

# ፍርሃት፣ ፈራ፣ የያህዌ ፍርሃት
“ፍርሃት” እና፣ “ፈራ” የሚሉት በእርሱ ወይም በሌሎች ላይ ጉዳት ይመጣል ብሎ ሲያስብ የሚኖረው ደስ የማይል ስሜት ነው።
* “ፍርሃት” ሥልጣን ላለው ሰው ጥልቅ አክብሮት መገለጫ ሊሆንም ይችላል።
* “የያህዌ ፍርሃት” (ወይም በተለመደው መልኩ፣ “የእግዚአብሔር ፍርሃት” እና፣ “የጌታ ፍርሃት”) ከልብ እግዚአብሔርን ማክበርንና ያንን በመታዘዝ ማሳየትን ያመለክታል። ይህ ዐይነቱ ፍርሃት እግዚአብሔር ቅዱስና ኀጢአትን የሚጠላ መሆኑን ከመገንዘብ የሚመጣ ነው።
* ያህዌን የሚፈራ ሰው ጠቢብ (አስተዋይ) እንደሚሆን መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።