# ፍርሃት፣ ፈራ፣ የያህዌ ፍርሃት “ፍርሃት” እና፣ “ፈራ” የሚሉት በእርሱ ወይም በሌሎች ላይ ጉዳት ይመጣል ብሎ ሲያስብ የሚኖረው ደስ የማይል ስሜት ነው። * “ፍርሃት” ሥልጣን ላለው ሰው ጥልቅ አክብሮት መገለጫ ሊሆንም ይችላል። * “የያህዌ ፍርሃት” (ወይም በተለመደው መልኩ፣ “የእግዚአብሔር ፍርሃት” እና፣ “የጌታ ፍርሃት”) ከልብ እግዚአብሔርን ማክበርንና ያንን በመታዘዝ ማሳየትን ያመለክታል። ይህ ዐይነቱ ፍርሃት እግዚአብሔር ቅዱስና ኀጢአትን የሚጠላ መሆኑን ከመገንዘብ የሚመጣ ነው። * ያህዌን የሚፈራ ሰው ጠቢብ (አስተዋይ) እንደሚሆን መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።