am_tw/bible/kt/favor.md

9 lines
1.2 KiB
Markdown

# ሞገስ፣ ሞገስ ያለው፣ አድልዎ (ከሌሎች የተለየ ሞገስ የሚደረግለት)
ሞገስ እርሱን በተመለከተ ጥሩ አመለካከት ያለንን ሰው ለመጥቀም የሚደረግ ነገርን ያመለክታለ። “ሞገስ ያለው” ነገር ቀና ተቀባይነት ያለው ወይም ጠቃሚ ነው።
* “አድልዎ” ለአንዱ ሞገስ ማሳየት ለሌላው ግን ሞገስ መንፈግ ነው። አንዳንዴ ሰዎች ሀብታም ወይ ታዋቂ በመሆናቸው ብቻ ከሌላው የተለየ ሞገስ (አድልዎ) ይደረግላቸዋል።
* ኢየሱስ፣ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት፣ “ሞገስ በማግኘት አደገ።” ይህም ፀባይና ባሕርዩ በእነርሱ ዘንድ ተቀባይነት ነበረው ማለት ነው።
* “ሞገስ አገኘ” የተሰኘው ፈሊጣዊ አነጋገር በሌሎች ዘንድ መወደድን ተቀባይነት ማግኘትን ያመልክታል።
* አንድ ንጉሥ ለሰው ሞገስ አደረገ ማለት ያ ሰው ያቀረበው ልመና በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት አገኘ ማለት ነው።