1.2 KiB
1.2 KiB
ሞገስ፣ ሞገስ ያለው፣ አድልዎ (ከሌሎች የተለየ ሞገስ የሚደረግለት)
ሞገስ እርሱን በተመለከተ ጥሩ አመለካከት ያለንን ሰው ለመጥቀም የሚደረግ ነገርን ያመለክታለ። “ሞገስ ያለው” ነገር ቀና ተቀባይነት ያለው ወይም ጠቃሚ ነው።
- “አድልዎ” ለአንዱ ሞገስ ማሳየት ለሌላው ግን ሞገስ መንፈግ ነው። አንዳንዴ ሰዎች ሀብታም ወይ ታዋቂ በመሆናቸው ብቻ ከሌላው የተለየ ሞገስ (አድልዎ) ይደረግላቸዋል።
- ኢየሱስ፣ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት፣ “ሞገስ በማግኘት አደገ።” ይህም ፀባይና ባሕርዩ በእነርሱ ዘንድ ተቀባይነት ነበረው ማለት ነው።
- “ሞገስ አገኘ” የተሰኘው ፈሊጣዊ አነጋገር በሌሎች ዘንድ መወደድን ተቀባይነት ማግኘትን ያመልክታል።
- አንድ ንጉሥ ለሰው ሞገስ አደረገ ማለት ያ ሰው ያቀረበው ልመና በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት አገኘ ማለት ነው።