am_tw/bible/kt/faithful.md

795 B

ታማኝ፣ ታማኝነት

ለእግዚአብሔር፣ “ታማኝ” መሆን ዘወትር በእርሱ ትምህርት መኖር ማለት ነው። ለእርሱ በመታዘዝ እውነተኛነትን ማሳየት ማለት ነው ታማኝ ሆኖ የመገኘት ሁኔታ፣ “ታማኝነት” ይባላል።

  • ታማኝ የሆነ ሰው ሁሌም ቃሉን እንደሚጠብቅና ለሌሎች ያለበትን ኅላፊነት ሁሌም እንደሚወጣ እምነት ሊጣልበት ይችላል።
  • ታማኝ ሰው ረጅምና አስቸጋሪ ቢሆንበት እንኳ በጀመረው ሥራ ይተጋል።
  • ለእግዚአብሔር ታማኝ መሆን ዘወትር እግዚአብሔር እንድናደርግ የፈለገውን በማድረግ መጽናት ነው።