# ታማኝ፣ ታማኝነት ለእግዚአብሔር፣ “ታማኝ” መሆን ዘወትር በእርሱ ትምህርት መኖር ማለት ነው። ለእርሱ በመታዘዝ እውነተኛነትን ማሳየት ማለት ነው ታማኝ ሆኖ የመገኘት ሁኔታ፣ “ታማኝነት” ይባላል። * ታማኝ የሆነ ሰው ሁሌም ቃሉን እንደሚጠብቅና ለሌሎች ያለበትን ኅላፊነት ሁሌም እንደሚወጣ እምነት ሊጣልበት ይችላል። * ታማኝ ሰው ረጅምና አስቸጋሪ ቢሆንበት እንኳ በጀመረው ሥራ ይተጋል። * ለእግዚአብሔር ታማኝ መሆን ዘወትር እግዚአብሔር እንድናደርግ የፈለገውን በማድረግ መጽናት ነው።