am_tw/bible/kt/evangelism.md

9 lines
1013 B
Markdown

# ወንጌላዊ
“ወንጌላዊ” የኢየሱስ ክርስቶስን የምሥራች(ወንጌል) ለሰዎች የሚናገር ሰው ነው።
* የ “ወንጌላዊ” ቃል በቃል ትርጉም፣ “የኢየሱስ ክርስቶስን የምሥራች የሚሰብክ ሰው ማለት ነው።”
* በኢየሱስና መስቀል ላይ በከፈለው የኀጢአት መሥዋዕት በማመን የእግዚአብሔር መንግሥት አካል እንደሚሆኑ ለሰዎች የምሥራቹን እንዲናገሩ ኢየሱስ አሥራ ሁለቱን ሐዋርያት ላከ።
* ክርስቲያኖች ሁሉ ይህን የምሥራች እንዲያካፍሉ ተነግሯቸዋል።
* አንዳንድ ክርስቲያኖች ውጤታማ በሆነ ሁኔታ ወንጌልን ለሌሎች የማካፈል ልዩ መንፈሳዊ ስጦታ ታድለዋል። እንዲህ ያሉ ሰዎች ወንጌል የማዳረስ ስጦታ አላቸው፤ “ወንጌላዊ” ተብለውም ይጠራሉ።