1013 B
1013 B
ወንጌላዊ
“ወንጌላዊ” የኢየሱስ ክርስቶስን የምሥራች(ወንጌል) ለሰዎች የሚናገር ሰው ነው።
- የ “ወንጌላዊ” ቃል በቃል ትርጉም፣ “የኢየሱስ ክርስቶስን የምሥራች የሚሰብክ ሰው ማለት ነው።”
- በኢየሱስና መስቀል ላይ በከፈለው የኀጢአት መሥዋዕት በማመን የእግዚአብሔር መንግሥት አካል እንደሚሆኑ ለሰዎች የምሥራቹን እንዲናገሩ ኢየሱስ አሥራ ሁለቱን ሐዋርያት ላከ።
- ክርስቲያኖች ሁሉ ይህን የምሥራች እንዲያካፍሉ ተነግሯቸዋል።
- አንዳንድ ክርስቲያኖች ውጤታማ በሆነ ሁኔታ ወንጌልን ለሌሎች የማካፈል ልዩ መንፈሳዊ ስጦታ ታድለዋል። እንዲህ ያሉ ሰዎች ወንጌል የማዳረስ ስጦታ አላቸው፤ “ወንጌላዊ” ተብለውም ይጠራሉ።