am_tw/bible/kt/command.md

809 B

ማዘዝ፣ ትእዛዝ

ማዘዝ ማለት አንዳች ነገርን እንዲያደርጉ ወይም እንዳያደርጉ ለሰዎች መናገር ማለት ነው። ትእዛዝ የሚባለው እንዲያደርጉ ወይም እንዳያደርጉ ለሰዎች የተሰጠው መመሪያ ነው።

  • ምንም እንኳ እነዚህ ቃሎች በመሠረቱ ተመሳሳይ ቢሆኑም፣ ብዙውን ጊዜ “ትእዛዝ” የሚለው ቃል የበለጠ መድበኛና ቋሚ የሆኑ የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ያመለክታል፤ ለምሳሌ “አሥሩ ትእዛዞች።”
  • አንድ ትእዛዝ አዎንታዊ (ለምሳሌ፣ “ወዳጆችን አክብር”) ወይም አሉታዊ፣ (ለምሳሌ፣ “አትስረቅ”) ሊሆን ይችላል።