# ማዘዝ፣ ትእዛዝ ማዘዝ ማለት አንዳች ነገርን እንዲያደርጉ ወይም እንዳያደርጉ ለሰዎች መናገር ማለት ነው። ትእዛዝ የሚባለው እንዲያደርጉ ወይም እንዳያደርጉ ለሰዎች የተሰጠው መመሪያ ነው። * ምንም እንኳ እነዚህ ቃሎች በመሠረቱ ተመሳሳይ ቢሆኑም፣ ብዙውን ጊዜ “ትእዛዝ” የሚለው ቃል የበለጠ መድበኛና ቋሚ የሆኑ የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ያመለክታል፤ ለምሳሌ “አሥሩ ትእዛዞች።” * አንድ ትእዛዝ አዎንታዊ (ለምሳሌ፣ “ወዳጆችን አክብር”) ወይም አሉታዊ፣ (ለምሳሌ፣ “አትስረቅ”) ሊሆን ይችላል።