am_tw/bible/kt/christ.md

1.5 KiB

ክርስቶስ፣ መሲሕ

“መሲሕ” ወይም፣ “ክርስቶስ” የሚለው ቃል፣ “የተቀባ” ማለት ሲሆን፣ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስን ነው የሚያመለክተው።

  • በሕዝቡ ላይ እንደ ንጉሥ እንዲገዛና ከኃጢአትና ከሞት እንዲያድናቸው እግዚአብሔር የሾመውን የእግዚአብሔር ልጅ ለማመልከት አዲስ ኪዳን ውስጥ፣ “መሲሕ” እና “ክርስቶስ” የተሰኙት ቃሎች ጥቅም ላይ ውለዋል፥
  • የብሉይ ኪዳን ነቢያት እርሱ ወደዚህ ምድር ከመምጣቱ በመቶ በሚቆጠሩ ዓመታት በፊት ስለ መሲሑ ትንቢት ጽፈዋል።
  • የሚመጣውን መሲሕ ለማመልከት፣ “የተቀባ” የሚል ትርጕም ያለው ቃል ብሉይ ኪዳን ውስጥ ተጠቅሷል።
  • ኢየሱስ ከእነዚህ ትንቢቶች ብዙዎችን ፈጸም፤ እርሱ መሲሕ መሆኑን የሚያረጋግጡ ተአምራትንም አደረገ፤ የተቀሩት ትንቢቶች የሚፈጸሙት እርሱ እንደ ገና ሲመለስ ነው።
  • “እርሱ ክርስቶስ” እና፣ “ክርስቶስ ኢየሱስ” ከተሰኙት ቃሎች መመልከት እንደሚቻለው፣ “ክርስቶስ” የሚለው እንደ መጠሪያ ጥቅም ላይ ውሏል።
  • “ኢየሱስ ክርስቶስ” እንደ ተሰኘው፣ “ክርስቶስ” የእርሱም አንድ አካል ሆኗል።