# ክርስቶስ፣ መሲሕ “መሲሕ” ወይም፣ “ክርስቶስ” የሚለው ቃል፣ “የተቀባ” ማለት ሲሆን፣ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስን ነው የሚያመለክተው። * በሕዝቡ ላይ እንደ ንጉሥ እንዲገዛና ከኃጢአትና ከሞት እንዲያድናቸው እግዚአብሔር የሾመውን የእግዚአብሔር ልጅ ለማመልከት አዲስ ኪዳን ውስጥ፣ “መሲሕ” እና “ክርስቶስ” የተሰኙት ቃሎች ጥቅም ላይ ውለዋል፥ * የብሉይ ኪዳን ነቢያት እርሱ ወደዚህ ምድር ከመምጣቱ በመቶ በሚቆጠሩ ዓመታት በፊት ስለ መሲሑ ትንቢት ጽፈዋል። * የሚመጣውን መሲሕ ለማመልከት፣ “የተቀባ” የሚል ትርጕም ያለው ቃል ብሉይ ኪዳን ውስጥ ተጠቅሷል። * ኢየሱስ ከእነዚህ ትንቢቶች ብዙዎችን ፈጸም፤ እርሱ መሲሕ መሆኑን የሚያረጋግጡ ተአምራትንም አደረገ፤ የተቀሩት ትንቢቶች የሚፈጸሙት እርሱ እንደ ገና ሲመለስ ነው። * “እርሱ ክርስቶስ” እና፣ “ክርስቶስ ኢየሱስ” ከተሰኙት ቃሎች መመልከት እንደሚቻለው፣ “ክርስቶስ” የሚለው እንደ መጠሪያ ጥቅም ላይ ውሏል። * “ኢየሱስ ክርስቶስ” እንደ ተሰኘው፣ “ክርስቶስ” የእርሱም አንድ አካል ሆኗል።