am_tw/bible/kt/blood.md

1.1 KiB

ደም

“ደም” ጉዳት ወይም ቁስል ሲኖር ከአንድ ሰው ቆዳ የሚወጣ ቀይ ፈሳሽ ነገርን ያመለክታል። ደም ለሰው አካል ሕይወት ሰጪ ምግብን ያመጣል።

  • ደም የሕይወት ምሳሌ ነው፤ የደም መፍሰስ የሕይወት መጥፋት ወይም የሞት ምሳሌ ነው።
  • ሰዎች ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ሲያቀርቡ እንስሳ ያርዱና ደሙን መሠዊያው ላይ ያፈስሱ ነበር። ይህም ለሰዎች ኃጢአት ክፍያ እንዲሆን የእንስሳው ሕይወት መሥዋዕት የመሆኑ ምስላ ነበር።
  • በመስቀል ላይ ሞቱ የኢየሱስ ደም ሰዎችን ከኃጢአታቸው የነጻቸዋል፤ ለኃጢአታቸው ይገባቸው የነበረው ቅጣት የመከፈሉ ምሳሌ ነው።
  • “ሥጋና ደም” የሰው ልጆችን የሚመለከት ፈሊጣዊ አንጋገር ነው።
  • “ሥጋና ደም” በዝምድና የተሳሰሩ ሰዎችን የሚመለከት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው።