# ደም “ደም” ጉዳት ወይም ቁስል ሲኖር ከአንድ ሰው ቆዳ የሚወጣ ቀይ ፈሳሽ ነገርን ያመለክታል። ደም ለሰው አካል ሕይወት ሰጪ ምግብን ያመጣል። * ደም የሕይወት ምሳሌ ነው፤ የደም መፍሰስ የሕይወት መጥፋት ወይም የሞት ምሳሌ ነው። * ሰዎች ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ሲያቀርቡ እንስሳ ያርዱና ደሙን መሠዊያው ላይ ያፈስሱ ነበር። ይህም ለሰዎች ኃጢአት ክፍያ እንዲሆን የእንስሳው ሕይወት መሥዋዕት የመሆኑ ምስላ ነበር። * በመስቀል ላይ ሞቱ የኢየሱስ ደም ሰዎችን ከኃጢአታቸው የነጻቸዋል፤ ለኃጢአታቸው ይገባቸው የነበረው ቅጣት የመከፈሉ ምሳሌ ነው። * “ሥጋና ደም” የሰው ልጆችን የሚመለከት ፈሊጣዊ አንጋገር ነው። * “ሥጋና ደም” በዝምድና የተሳሰሩ ሰዎችን የሚመለከት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው።