am_tw/bible/kt/bless.md

932 B

መባረክ፣ ተባረክ፣ በረከት

አንድ ሰው ወይም አንድ ነገር፣ “መባረክ” በዚያ ሰው ወይም ነገር ላይ መልካምና ጠቃሚ ነገር እንዲሆን ማድረግ ማለት ነው።

  • አንድን ሰው መባረክ በዚያ ሰው ላይ ጠቃሚ እና ቀና ነገር እንዲሆን ምኞትን መግለጽም ነው።
  • መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ጊዜ አባት ለልጆቹ የበረከት ቃል ይናገር ነበር።
  • ሰዎች እግዚአብሔርን “ሲባርኩ” ወይም እግዚአብሔር እንዲባረክ ምኞታቸውን ሲገልጹ እርሱን እያመሰገኑ ነው ማለት ነው።
  • “መባረክ” የሚለው ቃል ምግብ ከመበላቱ በፊት እንዲቀደስ ወይም ስለዚያ ምግብ እግዚአብሔርን ለማመስገን ጥቅም ላይ ይውላል።