# መባረክ፣ ተባረክ፣ በረከት አንድ ሰው ወይም አንድ ነገር፣ “መባረክ” በዚያ ሰው ወይም ነገር ላይ መልካምና ጠቃሚ ነገር እንዲሆን ማድረግ ማለት ነው። * አንድን ሰው መባረክ በዚያ ሰው ላይ ጠቃሚ እና ቀና ነገር እንዲሆን ምኞትን መግለጽም ነው። * መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ጊዜ አባት ለልጆቹ የበረከት ቃል ይናገር ነበር። * ሰዎች እግዚአብሔርን “ሲባርኩ” ወይም እግዚአብሔር እንዲባረክ ምኞታቸውን ሲገልጹ እርሱን እያመሰገኑ ነው ማለት ነው። * “መባረክ” የሚለው ቃል ምግብ ከመበላቱ በፊት እንዲቀደስ ወይም ስለዚያ ምግብ እግዚአብሔርን ለማመስገን ጥቅም ላይ ይውላል።