am_tw/bible/kt/birthright.md

1.0 KiB

የመወለድ መብት

“የመወለድ መብት” የተሰኘው ቃል ከቤተ ሰቡ የተወለዱ የመጀመሪያ ወንድ ልጅ ያለውን ክብር፣ ከቤተ ሰቡ መጠራትንና ሀብት መወሰድን መደበኛ መብት ያመለክታል።

  • የመጀመሪያው ወንድ ልጅ ያለው የመወለድ መብት ዕጥፍ የአባቱን ሀብት የመውሰድ መብትንም ይጨምራል።
  • የአንድ ንጉሥ የመጀመሪያ ወንድ ልጅ አባቱ ከሞተ በኋላ ሥልጣኑን ወስዶ የመግዛት የመወለድ መብት አለው።
  • ኤሳው ብኵርናውን ወይም የመወለድ መብቱን ለታናሽ ወንድሙ ለያዕቆብ ሸጠ። ከዚህም የትነሣ ከኤሳው ይልቅ ያዕቆብ የመጀመሪያ ልጅ የሚያገኘውን በረከት ወሰደ።
  • የመወለድ መብት በቤተ ሰቡ የዘር ሐረግ ውስጥ የመጀምሪያ ሆኖ የመጠራት ክብርንም ይጨምራል።