am_tw/bible/kt/birthright.md

9 lines
1.0 KiB
Markdown
Raw Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# የመወለድ መብት
“የመወለድ መብት” የተሰኘው ቃል ከቤተ ሰቡ የተወለዱ የመጀመሪያ ወንድ ልጅ ያለውን ክብር፣ ከቤተ ሰቡ መጠራትንና ሀብት መወሰድን መደበኛ መብት ያመለክታል።
* የመጀመሪያው ወንድ ልጅ ያለው የመወለድ መብት ዕጥፍ የአባቱን ሀብት የመውሰድ መብትንም ይጨምራል።
* የአንድ ንጉሥ የመጀመሪያ ወንድ ልጅ አባቱ ከሞተ በኋላ ሥልጣኑን ወስዶ የመግዛት የመወለድ መብት አለው።
* ኤሳው ብኵርናውን ወይም የመወለድ መብቱን ለታናሽ ወንድሙ ለያዕቆብ ሸጠ። ከዚህም የትነሣ ከኤሳው ይልቅ ያዕቆብ የመጀመሪያ ልጅ የሚያገኘውን በረከት ወሰደ።
* የመወለድ መብት በቤተ ሰቡ የዘር ሐረግ ውስጥ የመጀምሪያ ሆኖ የመጠራት ክብርንም ይጨምራል።