am_tw/bible/kt/atonementlid.md

1.1 KiB

የስርየት መክደኛ

“የስርየት መክደኛ” ከወርቅ የተሠራ ጠፍጣፋ ነገር ሲሆን የታቦቱን የላይኛ ክፍል ለመሸፈን ጥቅም ላይ ይውል ነበር። አንዳንድ ትርጉሞች “የስርየት መሸፈኛ” ይሉታል

  • የስርየት መክደኛ 115 ሳንቲሜትር ርዝመትና 70 ሳንቲሜትር ስፋት ነበረው
  • ከስርየት መክደኛው በላይ ክንፎቻቸው እርስ በርስ የተነካኩ ሁለት የወርቅ ኪሩቤል ነበሩ
  • ከስርየት መክደኛው በላይ፥ ከተዘረጉት የኪሩቤል ክንፎች በታች ከእስራኤላውያን ጋር እንደሚገናኝ ያህዌ ተናግሮአል። እንደሕዝቡ ተወካይ ይህን ማድረግ የተፈቀደለት ሊቀ ካህኑ ብቻ ነበር
  • ይህ የስርየት መክደኛ አንዳንዴ፥ “የምሕረት መቀመጫ” ተብሎአል፤ እንዲህ የተባለበት ምክንያት ኃጢአተኛ የሰው ልጆችን ለመዋጀት የሚመጣው የእግዚአብሔር ምሕረት መተለለፊያ ስለሆነ ነው