am_tw/bible/kt/atonementlid.md

9 lines
1.1 KiB
Markdown
Raw Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# የስርየት መክደኛ
“የስርየት መክደኛ” ከወርቅ የተሠራ ጠፍጣፋ ነገር ሲሆን የታቦቱን የላይኛ ክፍል ለመሸፈን ጥቅም ላይ ይውል ነበር። አንዳንድ ትርጉሞች “የስርየት መሸፈኛ” ይሉታል
* የስርየት መክደኛ 115 ሳንቲሜትር ርዝመትና 70 ሳንቲሜትር ስፋት ነበረው
* ከስርየት መክደኛው በላይ ክንፎቻቸው እርስ በርስ የተነካኩ ሁለት የወርቅ ኪሩቤል ነበሩ
* ከስርየት መክደኛው በላይ፥ ከተዘረጉት የኪሩቤል ክንፎች በታች ከእስራኤላውያን ጋር እንደሚገናኝ ያህዌ ተናግሮአል። እንደሕዝቡ ተወካይ ይህን ማድረግ የተፈቀደለት ሊቀ ካህኑ ብቻ ነበር
* ይህ የስርየት መክደኛ አንዳንዴ፥ “የምሕረት መቀመጫ” ተብሎአል፤ እንዲህ የተባለበት ምክንያት ኃጢአተኛ የሰው ልጆችን ለመዋጀት የሚመጣው የእግዚአብሔር ምሕረት መተለለፊያ ስለሆነ ነው