am_tw/bible/kt/amen.md

1.1 KiB

አሜን፣በእውነት ይሁን

“አሜን” የሚለውለንድ ሰው የተናገረውን አጽንዖት ለመስጠት ወይም ትኩረት እንዲሰጠው ለማድረግ ጥቅም ላይ የሚውል ቃል ነው። ኢያሱስ ይህን ቃል ሲናገር ብዙውን ጊዜ አሜን ይሁን እንደ ማለት ነው።

  • ጸሎት መጨረሻ ላይ “አሜን” ከተባለ ከጸሎት ጋር መስማማትን ወይም ጸሎት እንዲፈጽም መፈለግን ያሳያል።
  • በትምህርቱ የተናገረውን ለማስረገጥ ኢየሱስ “አሜን” በሚለው ተጠቅሟል ብዙውን ጊዜ እንዲህ ያደርግ የነበረው ከተናገረው ጋር የሚያያዝ ሌላ ትምህርት ለማቅረብ፣ “እኔ እንዲህ እላችኋለው” በሚልበት ጊዜ ነው።
  • አንዳንድ የእንግሊዝኛ ትርጉሞች ይህን፣ በእውነት ይሁን በማለት ተርጉመውታል ለተወሰነ ነገር አጽንዖት ለመስጠት ይተነገረው ቅን ወይም እውነት መሆኑን ለመግለጥ ጥቅም ላይ ይውላል።