am_tw/bible/kt/altar.md

827 B

መሠዊያ

መሠዊያ ለእግዚአብሔር መባ(ስጦታ)እንዲሆን እስራኤላውያን እንስሳትና የእህል ዓይነቶችን የሚያቃጥልበት ከፍ ብሎ የሚሠራ ነገር ነው።

  • በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን የቦካ በመካብ ወይም ክምር እስኪሆን ድረስ ድንጋዮችን በመደርደር ቀለል ያሉ መሠዊያዎች ይሠሩ ነበር።
  • ከእንጨት ሳጥን መሰል መሠዊያዎች ይሠሩና በኋላ እንጨቱ ወርቅን፣ናስን ውይም መዳብን በመሳሰሉ ነገሮች ይለበጡ ነበር።
  • እስራኤላውያን በነበሩበት አካባቢ የነበሩት ሕዝቦችም ለአማልክቶቻቸው መዋዕት ማቅረቢያ መሠዊያዎች ይሠሩ ነበር።