1.1 KiB
1.1 KiB
ጸያፍ
- ርኩስ ወይም የተጠላ ነገርን ለመግላጽ “ጸያፍ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ ውሏል።
- ግብፃውያን የዕብራውያን ሰዎችን እንደ “ጸያፍ” ይቆጥሩ ነበር። ይህም ማለት ግብጻውያን ዕብራውያንን ይጠሏቸው ነበር፤ከእነርሱ ጋር ለመተባበር ወይም አጠገባቸው ለመሆን አይፈልጉም ነበር ማለት ነው።
- መጽሐፍ ቅዱስ “ለያህዌ ጸያፍ” ከሚላቸው ነገሮች ጥቂቶቹ ውሸት ትዕቢት፣ሰዎችን መስዋዕት አድርጎ ማቅረብ፣ጣዖት ማምለክ፣መግደል፣የዝሙት ኅጢአቶችና ከወንድ ጋር ግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸምን የመሳሰሉት ናቸው።
- የመጨረሻ ቀኖችን አስመልክቶ ለደቀ መዛሙርቱ ሲያስተምር ኢየሱስ በእግዚአብሔር ላይ በዓመፅ የአምልኮ ቦታውን ለማርከስ ስለማቆመው ትንቢተ ዳንኤል ላይ ያለውን፣ የጥፋት ርኩሰት አመልክቷል።