am_tw/bible/kt/abomination.md

7 lines
1.1 KiB
Markdown
Raw Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ጸያፍ
* ርኩስ ወይም የተጠላ ነገርን ለመግላጽ “ጸያፍ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ ውሏል።
* ግብፃውያን የዕብራውያን ሰዎችን እንደ “ጸያፍ” ይቆጥሩ ነበር። ይህም ማለት ግብጻውያን ዕብራውያንን ይጠሏቸው ነበር፤ከእነርሱ ጋር ለመተባበር ወይም አጠገባቸው ለመሆን አይፈልጉም ነበር ማለት ነው።
* መጽሐፍ ቅዱስ “ለያህዌ ጸያፍ” ከሚላቸው ነገሮች ጥቂቶቹ ውሸት ትዕቢት፣ሰዎችን መስዋዕት አድርጎ ማቅረብ፣ጣዖት ማምለክ፣መግደል፣የዝሙት ኅጢአቶችና ከወንድ ጋር ግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸምን የመሳሰሉት ናቸው።
* የመጨረሻ ቀኖችን አስመልክቶ ለደቀ መዛሙርቱ ሲያስተምር ኢየሱስ በእግዚአብሔር ላይ በዓመፅ የአምልኮ ቦታውን ለማርከስ ስለማቆመው ትንቢተ ዳንኤል ላይ ያለውን፣ የጥፋት ርኩሰት አመልክቷል።