am_tw/bible/other/haughty.md

13 lines
1.3 KiB
Markdown

# ዕቡይ
ዕቡይ ሰው ከሚገባው በላይ ስለ ራሱ ከፍ ያለ ግምት አለው።
* “ዕቡይ” የእብሪተኝነት ዝንባሌ ያለው፣ “ትዕቢተኛ” ሰው ነው።
* ስለ ራሱ በትዕቢት የሚያስብ ሰውን ለማመልከት መጽሐፍ ቅዱስ “ዕቡይ ዐይን” ወይም፣ “ዕቡይ አንገት” የተሰኙ አገላለጾች አሉት።
ከ . . . ጋር ግንኙነት፣ ከ . . . ጋር መተኛት፣ አብሮ ተኛ
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እነዚህ ቃሎች በተዘዋዋሪ ግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸምን የሚያመለክቱ ናቸው።
* ከአንድ ሰው ጋር መተኛት ከዚያ ሰው ጋር ግብረ ሥጋ መፈጸምን የሚመልከት የተለመደ አነጋገር ነው። የዚህ ኀላፊ ጊዜ፣ “አብሮ ተኛ” የሚለው ነው።
* “መሐልዩ መሓልይ ዘሰሎሞን” በተሰኘው የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ULB የተሰኘው ትርጕም፣ “ፍቅር መሥራት” ብሎታል፤ በዚያ ዐውድ ውስጥ፣ “ፍቅር” ግብረ ሥጋ ግንኙነትን ያመለክታል። ይህ፣ “ከ . . . ጋር ፍቅር መሥራት” ከሚለው አገላለጽ ጋር ይገናኛል።