# ዕቡይ ዕቡይ ሰው ከሚገባው በላይ ስለ ራሱ ከፍ ያለ ግምት አለው። * “ዕቡይ” የእብሪተኝነት ዝንባሌ ያለው፣ “ትዕቢተኛ” ሰው ነው። * ስለ ራሱ በትዕቢት የሚያስብ ሰውን ለማመልከት መጽሐፍ ቅዱስ “ዕቡይ ዐይን” ወይም፣ “ዕቡይ አንገት” የተሰኙ አገላለጾች አሉት። ከ . . . ጋር ግንኙነት፣ ከ . . . ጋር መተኛት፣ አብሮ ተኛ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እነዚህ ቃሎች በተዘዋዋሪ ግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸምን የሚያመለክቱ ናቸው። * ከአንድ ሰው ጋር መተኛት ከዚያ ሰው ጋር ግብረ ሥጋ መፈጸምን የሚመልከት የተለመደ አነጋገር ነው። የዚህ ኀላፊ ጊዜ፣ “አብሮ ተኛ” የሚለው ነው። * “መሐልዩ መሓልይ ዘሰሎሞን” በተሰኘው የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ULB የተሰኘው ትርጕም፣ “ፍቅር መሥራት” ብሎታል፤ በዚያ ዐውድ ውስጥ፣ “ፍቅር” ግብረ ሥጋ ግንኙነትን ያመለክታል። ይህ፣ “ከ . . . ጋር ፍቅር መሥራት” ከሚለው አገላለጽ ጋር ይገናኛል።