19 lines
2.4 KiB
Markdown
19 lines
2.4 KiB
Markdown
# የተስፋ ምድር
|
|
|
|
“የተስፋ ምድር” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች እንጂ በጠቅላላው መጽሐፍ ቅዱስ አይደለም። ለአብርሃምና ለዘሮቹ እንደሚሰጥ እግዚአብሔር ቃል የገባላት የምድረ ከነዓን አማራጭ ቃል ነው።
|
|
|
|
* አብራም በዑር ከተማ በነበረ ጊዜ እንዲሄድና በከነዓን ምድር እንዲኖር እግዚአብሔር አዘዘው። እርሱና የእርሱ ዘሮች የሆኑት እስርኤላውያን ለብዙ ዓመታት እዚያ ኖሩ።
|
|
* እዚያ ከደረሰው ድርቅ የተነሣ ራብ በሆነ ጊዜ እስራኤላውያን ወደ ግብፅ ሄዱ።
|
|
* ክአራት መቶ ዓመት በዓላ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከግብፅ ባርነት አውጥቶ እንደሚሰጣቸው እግዚአብሔር ወደ ገባላቸው ምድር ወደ ምድረ ከነዓን አመጣቸው።
|
|
|
|
ነቢይ፣ ትንቢት፣ ትንቢት ተናገረ፣ ተመልካች፣ ነቢዪት
|
|
“ነቢይ” የእግዚአብሔርን መልእክት ለሰዎች የሚናገር ሰው ነው። ይህን የምታደርግ ሴት ነቢዪት ትባላለች።
|
|
|
|
* ነቢይ የሚለው የቀድሞ መጠሪያ፣ “ተመልካች” ሲሆን፣ “የሚያይ፣ የሚመለከት ሰው” ማለት ነው።
|
|
* ይሁን እንጂ “ተመልካች” የሚለው ቃል አንዳንዴ ሟርተኛን ወይም ሐሰተኛ ነቢይንም ያመለክታል።
|
|
* ምንጊዜም ነቢያት ሰዎች በኀጢአታቸው እንዲመለሱና ለእግዚአብሔር እንዲታዘዙ ያስጠነቅቃሉ።
|
|
* “ትንቢት” ነቢዩ የሚናገረው መልእክት ነው። “ትንቢት መናገር” የእግዚአብሔርን መልእክት መናገር ማለት ነው።
|
|
* ብዙውን ጊዜ የትንቢት መልእክት ወደ ፊት የሚሆነውን ያመለክታል።
|
|
* ብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉ ብዙ ትንቢቶች ተፈጽመዋል።
|
|
* “ሐሰተኛ ነቢይ” በአልን ከመሳሰሉ ሐሰተኛ አማልክት ተቀብያለሁ የሚለውን መልእክት የሚናገር ወይም የእግዚአብሔር መልእክት እንደ ተቀበለ በውሸት የሚናገር ሰው ነው።
|